ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ድረገጽ ነበረ …
እሺ …
እሺ አትበል … ሞዛዛ … ዝም ብለህ አዳምጥ …
እሺ
ፈንዳ እሺ!
አልፈነዳም
ጥሩ …
ቀጥል ተረቱን … ይቅርታ … እሺ አልልም
… ቀጠልኩ
አንድ ድረገጽ ነበር … ድረገጹ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታይ ከመታገዱ በፊት አንዳንድ የምጽፋቸውን ነገሮች ከብሎጌ ላይ ተውሶ ለታዳሚዎቹ ያካፍል ነበር … ከዚያ ከለታት ባንዱ ቀን አዲስ አበባ ያሉት ሰዎች ያግዱታል … የገረመኝ ነገር መታገዱ ሳይሆን ልክ እኔ ያገድኩት ይመስል የምጽፋቸውን ነገሮች እንደ ድሮው ከማካፈል መታቀቡ ነው … ሊገባኝ አልቻለም … ተረቴን መልሱ አፌን በእንኮይ አብሱ አለች ቆንጅዬ ልጅ … ቢሆንም ቢሆንም አሉ ሃምሳ አለቃ ገብሩ … እኔ ደንታ የለኝም
ተረትህ አለቀ?
አለቀ
ሌላ ተረት ጨምር እስኪ …
ሌላ ተረት ካማረህ ተረት ሰፈር ሂድ … ቆሪጥና አጋፋሪ እንደሻው በጋሽ ስብሐት አንደበት ያዝናኑሃል
ደረቅ
ayzoh, atibesacH!
Ere jelese … yemin mebesachet!
Endew lemetenfes yahil naw …